Montgomery Cares
 

ሞንትጎመሪ ኬርስ ምንድ ነው?

ሞንትጎመሪ ኬርስ የሕክምና ዋስትና ለሌላቸው፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ለአቅመ አዳም ለደረሱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች መሰረታዊ የጤና አገልግሎት የሚሰጥ መርሃግብር ነው። ይህ መርሃግብር አለትርፍ አገልግሎት ለሚሰጡ ነጻ ክሊኒኮች ማህበርን ለመደገፍ በሞንትጎመሪ ካውንቲ በከፊል የገንዘብ ድጎማ ይደረግለታል።

እነዚህ ክሊኒኮች በመንግስት አይተዳደሩም። እያንዳንዱ ክሊኒክ የራሱ የሆነ ታሪክ፣ ባህል፣ ልምድና የገቢ ምንጭ አለው። ክሊኒኮቹ ሁሉ የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች አሉዋቸው።

የሚያስፈልጉትዎትን የጤና ጥበቃ አገልግሎት ያግኙ

የጤና እንክብካቤ ያስፈልግዎታል። ነገር ግን የሕክምና ዋስትና የለዎትም። በሞንትጎመሪ ካውንቲ ኗሪ ከሆኑ ጥሩ መሰረታዊ የጤና ጥበቃ አገልግሎት በማንኛውም ሞንትጎመሪ ኬርስ በሚረዳው ክሊኒክ ማግኘት ይችላሉ። መስፈርቱን ለሚያሟሉ ሰዎች እነዚህ ክሊኒኮች የጤና ጥበቃ አገልግሎቶችን በነጻ ወይም በዝቅተኛ ዋጋ ይሰጣሉ።

ሞንትጎመሪ ኬርስ በሞንትጎመሪ ካውንቲ በከፊል የገንዘብ ድጎማ ይደረግለታል

© ሞንትጎመሪ ኬርስ። ሞንትጎመሪ ኬርስ በሞንትጎመሪ ካውንቲ በከፊል የገንዘብ ድጎማ ይደረግለታል. የግለህይወት ፖሊሲ.